Tsehay Bank SC Call For Exam
Tsehay Bank SC, established by 734 million birr paid up capital and 2.8 billion birr subscribed capital. The Bank held its first general assembly in Sheraton Addis Hotel on Feb 18, 2021
The Bank will strive to satisfy stakeholders’ by ensuring service excellence that appeal to the ever-diversifying and growing needs of customers. The term, “Tsehay” is an Amharic word that denotes “The Sun,” and our motto is “For All,” referring to our financial inclusion objective.
Tsehay Bank SC Call For Exam
ፀሐይ ባንክ ለትሬኒ ባንከር የሥራ ዘርፍ አመልክታችሁ የመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ የOnline ፈተና ላልተፈተናችሁ አመልካቾች በሙሉ!
ፀሐይ ባንክ በትሬኒ ባንከር የሥራ ዘርፍ ለመቀጠር ላመለከታችሁ ተወዳዳሪዎች የመጀመሪያ ዙር የማጣሪያ ፈተና ከኦክቶበር 20 እስከ 27/ 2022 መሰጠቱ ይታወሳል። ሆኖም ፈተናውን በተለያየ ምክንያት ሳትፈተኑ የቀራችሁ አመልካቾች አንድ የመጨረሻ ተጨማሪ ዕድል እንድታገኙ ተወስኗል። ስለዚህ
1. ወደፈተና የሚወስደው ማስፈንጠሪያ (link) በሰዓቱ ባለመድረሱ ፈተናውን መፈተን ያልቻላችሁ
2. የደረሰው ማስፈንጠሪያ (link) ወደፈተናው ሳይወስዳችሁ ቀርቶ ፈተናውን መፈተን ያልቻላችሁ
3. በኔትወርክ መቆራረጥ ምክንያት ፈተናውን በተሰጠው ሰዓት መጨረስ ያልቻላችሁ
4. ፈተናውን መጀመሪያ ስታመለክቱ ባስመዘገባችሁት የኢሜይል አድራሻ ሳይሆን በሌላ አድራሻ የተፈተናችሁ
አመልካቾች በሙሉ ሐሙስ ኖቬምበር 17/2022 ረፋድ 4 ሰዓት ላይ የመጨረሻ ዙር ፈተና ስለሚሰጥ ይህንን ፈተና እንድትፈተኑ እናሳስባለን።
ጠቃሚ መረጃዎች
1. ስታመለክቱ ያስመዘገባችሁትን የኢሜይል አድራሻ የማታውቁ/የማታስታውሱ አመልካቾች ከፈተናው ቀን አስቀድሞ ኢሜይል አድራሻችሁን ማረጋገጥ ወይንም በአቅራቢያችሁ በሚገኝ የፀሐይ ባንክ ቅርንጫፍ ወይንም በዋናው መሥሪያ ቤት ማንነታችሁን የሚገልፅ መታወቂያ በመያዝ የኢሜይል አድራሻችሁን ማስተካከል ይገባችኋል።
2. ፈተናው በሚሰጥበት ቀን እና ሰዓት አስተማማኝ የኢንተርኔት ኮኔክሽን ያለበት ቦታ ሆናችሁ ፈተናውን መውሰድ ይገባችኋል።
3. ፈተናው የሚሰጠው ከዚህ ቀደም የተሰጠውን ፈተና ላልወሰዱ እና በሌላ የኢሜይል አድራሻ ለተፈተኑት ብቻ ነው። ከዚህ ቀደም ፈተናውን ባስመዘገባችሁት የኢሜይል አድራሻ ተፈትናችሁ ውጤታችሁን ያወቃችሁ አመልካቾች ፈተናውን ለሁለተኛ ጊዜ መፈተን አይገባችሁም። ሁለተኛ ጊዜ ፈተናውን ተፈትናችሁ የምትገኙ አመልካቾች ማመልከቻችሁ ሙሉ በሙሉ ከውድድር ውጪ እንደሚሆን እናሳስባለን።
ሐሙስ ኖቬምበር 17/2022 ከሚሰጠው ፈተና ሌላ በምንም ምክንያት ሌላ ዕድል ስለማይኖር አመልካቾች የተሰጡ መመሪያዎችን በሚገባ በመተግበር ፈተናውን እንድትወስዱ እናሳስባለን።
ፀሐይ ባንክ